Mezmur Wiki
Register
Advertisement
ይህ ፡ ድህረ-ገጽ ፡ ወደ ፡ WikiMezmur.org ፡ ተዘዋውሯል ። እባክዎን ፡ ይጎብኙት ።
This website has been transferred to WikiMezmur.org, Please Visit.

ለውድቀት ፡ መሮጤ ፡ ምንድነው

ማዳንህ ፡ የገባኝ ፡ ጥንት ፡ ነው

አባቴ ፡ ልጄ ፡ አንቺ ፡ የኔ ፡ እያልክ

የጎረቤት ፡ ኑሮዬ ፡ ናፈቀኝ

ጥፋቱ ፡ ከጠላት ፡ ወይ ፡ ከኔ

ገብቶኝ ፡ እንዳልገባው ፡ መሆኔ

አመል ፡ ካልሆነብኝ ፡ በስተቀር

አሁን ፡ ምን ፡ ይገኛል ፡ ጠላት ፡ ሰፈር


[አግዘኝ ፡ ደግፈኝ

ብቻዬን ፡ አቅም ፡ የለኝ

ያየህልኝን ፡ ቁም ፡ ነገር

እንዳላጣው ፡ በተራ ፡ ነገር] /፪


ማን ፡ አየኝ ፡ አላየኝ ፡ ኑሮዬን

አልደብቀው ፡ ካንተ ፡ ገበናዬን

ሰው ፡ ፈርቶ ፡ ሰው ፡ ሸሽቶስ ፡ እስከመቼ

ልኑር ፡ መጀመሪያ ፡ አንተን ፡ ፈርቼ

እንዳልሞት ፡ ነበረ ፡ መዳኔ

ፈቅደህ ፡ የሞትክልኝ ፡ ካህኔ

እያወኩ ፡ ከገባሁ ፡ ከእሳቱ

ማን ፡ ሊመልሰኝ ፡ ነው ፡ ማን ፡ ብርቱ


[አግዘኝ ፡ ደግፈኝ

ብቻዬን ፡ አቅም ፡ የለኝ

ያየህልኝን ፡ ቁም ፡ ነገር

እንዳላጣው ፡ በተራ ፡ ነገር] /፪


ነጻነቴም ፡ በዛ ፡ መሰለኝ

ምን ፡ አለበት ፡ ኑሮ ፡ ለመደኝ

ቀለለኝ ፡ የጥፋት ፡ መንገዴ

ላይቀርልኝ ፡ ካለፈ ፡ መንደዴ

የማውቀውን ፡ እውነት ፡ ሳልገፋ

ከበር ፡ መልስ ፡ ሳልሆን ፡ ሳልጠፋ

ብላቴናነቴን ፡ ታደገው

አውለው ፡ ከቤትህ ፡ ከሚበጀው


[አግዘኝ ፡ ደግፈኝ (ደግፈኝ)

ብቻዬን ፡ አቅም ፡ የለኝ (ብቻዬን----አቅም ፡ የለኝ)

ያየህልኝን ፡ ቁም ፡ ነገር (ያየህልኝን----ቁም ፡ ነገር)

እንዳላጣው ፡ በተራ ፡ ነገር] /፪ (እንዳላጣው----ተራ ፡ ነገር)


thumb|400px|right|ሃና ተክሌ (Hana Tekle) - አግዘኝ (Agizegne) መደብ:አማርኛ (Amharic) መደብ:ሃና ተክሌ (Hana Tekle)

Advertisement