Mezmur Wiki
Register
Advertisement
ይህ ፡ ድህረ-ገጽ ፡ ወደ ፡ WikiMezmur.org ፡ ተዘዋውሯል ። እባክዎን ፡ ይጎብኙት ።
This website has been transferred to WikiMezmur.org, Please Visit.

መስፍን ፡ ጉቱ ፡ አንተ ፡ የኔ ( Mesfin Gutu - Ante Yenae)

አንተ ፡ የኔ ፡ የራሴ ፡ የግሌ ፡ የኔ

ባስጨናቂው ፡ ለት ፡ ለኔ ፡ ደርሰህ

በጨለማ ፡ እኔ ፡ ላይ ፡ ብርሃን ፡ ይብራ ፡ ብለህ

ታሪኬን ፡ ለውጠህ ፣ ታዲያ ፡ ልበልህ ፡ እንጂ ፡ አንተ ፡ የኔ ። /፪


ማን ፣ ማን ፣ ማን ይወስድብኛል አንተን ከኔ /፪

ተማመለህ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ጌታ

በጭንቅ ፡ የወለድከኝ ፡ በጎልጎታ

እድሜዬን ፡ በሙሉ ፡ ሰጥሃለሁ

በዚህ ፡ ዓለም ፡ ለቃልህ ፡ እገዛለሁ ፣ እገዛለሁ ።


ታዲያ ፣ ልዘምር ፡ እንጂ ፡ ልቀኝ ፡ እንጂ

ለባለውለታዬ ፡ ልኑር ፡ እንጂ ፣ ታዲያ ፡ ታዲያ /፪


እንደመሸ ፡ አይቀርም ፡ ሌሊቱ ፡ ይነጋል /፬

ማንጋት ፡ ልማድህ ፡ ነውና ፣ ማንሳት ፡ ልማድህ ፡ ነወና

ማክበር ፡ ልማዲህ ፡ ነወና ፣ ማስዋብ ፡ ልማድህ ፡ ነውና ።


ውዴ ፡ የኔ ፡ ነው ፡ እኔም ፡ ደግሞ ፡ የእርሱ ፡ ነኝ ፡ የየሱስ ፡ነኝ /፪

ማንም ፡ አይገባም ፡ በመሀላችን ።።???።።።። የሌለበት ፡ ነው ፡ ፍቅራችን

ጊዜም ፡ ሁኔታም ፡ አይሽረዉም ፡ ለኔስ ፡ እየሱሴ ፡ ልዩ ፡ ነዉ ፣ ልዩ ፡ ነዉ

ታዲያ ፣ ልዘምር ፡ እንጂ ፡ ልቀኝ ፡ እንጂ

ለባለውለታዬ ፡ ልኑር ፡ እንጂ ፣ ታዲያ ፡ ታዲያ ። /፪


አንተ ፡ የኔ ፡ የራሴ ፡ የግሌ ፡ የኔ

ባስጨናቂው ፡ ለት ፡ ለኔ ፡ ደርሰህ

በጨለማ ፡ እኔ ፡ ላይ ፡ ብርሃን ፡ ይብራ ፡ ብለህ

ታሪኬን ፡ ለውጠህ ፣ ታዲያ ፡ ልበልህ ፡ እንጂ ፡ አንተ ፡ የኔ ። /፪

am.mezmur.wikia.com


thumb|402px|right|መስፍን ጉቱ : አንተ የኔ ( Mesfin Gutu - Ante Yenae) መደብ:አማርኛ (Amharic) መደብ:መስፍን ጉቱ (Mesfin Gutu)

Advertisement