FANDOM


ይህ ፡ ድህረ-ገጽ ፡ ወደ ፡ WikiMezmur.org ፡ ተዘዋውሯል ። እባክዎን ፡ ይጎብኙት ።
This website has been transferred to WikiMezmur.org, Please Visit.

የሰው ፡ ሁሉ ፥ ልብ ፡ ተማርኮለታል

ነገም ፡ ንግስና ፥ ይጠብቀዋል ፤

እኔ ፡ እተካለሁ ፥ በአንተ ፡ ቦታ

ፍጠን ፡ አባቴ ፥ በል ፡ በርታ ፡ በርታ ።


አንድ ፡ ያላሰበ ፥ ያልተማከረ

አንድ ፡ ወዳጅ ፡ አየሁ ፥ ፍቅር-ያከበረ ፤

ነፍስን ፡ የሚሹ ፡ አሉ ፥ በደጅ

የሚል-አድምጥ፥ ሂድ ፡ ብለጥ ፡ እንጂ ።


ኦ ፥ እግዚአብሔር ፡ ሆይ

ይህ ፡ ሰው ፥ ማረከኝ ፤

ንጹህ ፡ ልብን ፥ ፍጠርልኝ

ለወዳጄ ፥ ታማኝ ፡ አርገኝ ፡ አርገኝ።


ኦ ፥ እግዚአብሔር ፡ ሆይ

ይህ ፡ ሰው ፥ ማረከኝ ፤

ንጹህ ፡ ልብን ፥ ፍጠርልኝ

ለወንድሜ ፥ ቀና ፡ አርገኝ ፣ አርገኝ።


ምን ፡ እንዳሰበ ፥ ሳይረዳዉ

ወዳጄ ፡ ብሎ ፥ ሲያስከትለዉ ፤

ልቡ ፡ ሲገለጥ ፥ ሆኔበት ፡ ባዳ

አቅፎ ፡ እየሳመ ፥ ሸጠው ፡ ይሁዳ ።


ሳይ-ለይ ፣ ሳይ-ለይ፥ አብሮ መብላቱ

ሳይ-ለይ ፣ ሳይ-ለይ ፥ መጫወቱ ፤

ሳይ-ለይ ፣ ሳይ-ለይ ፥ ያሳለፍካቸው

ሳይ-ለይ ፣ ሳይ-ለይ ፥ በትግል ፡ ናቸው ።


ኦ ፡ ይሁዳ ፥ ኧረ ፡ ተው ፡ ይሁዳ

ተው ፡ ይሁዳ ፥ አትሁን ፡ እንግዳ ፤

ሸጠህ ፡ ጥለህ ፥ ወዳጅነትህን

አትግዛበት ፥ የደም ፡ ምህረት ።


ተው ፡ ይሁዳ ፡ ኧረ ፡ ተው ፡ ይሁዳ

ተው ፡ ይሁዳ ፡ አትሁን ፡ እንግዳ ፤

ሸጠህ ፡ ጥለህ ፡ ወዳጅነትህን

አትግዛበት ፡ የደም ፡ ምህረት ።


ኦ ፡ እግዚአብሔር ፡ ሆይ ( እግዚአብሔር ፡ ሆይ )

ምህረት ፡ አርግልኝ ( ምህረት ፡ አርግልኝ ) ፤

ንጹህ ፡ ልብን ፥ ፍጠርልኝ

ለወዳጄ፥ ታማኝ ፡ አርገኝ (ታማኝ ------ አርገኝ ) ።


[ ኦ ፡ እግዚአብሔር ፡ ሆይ ( እግዚአብሔር ፡ ምሕረት )

ምህረት ፡ አርግልኝ ( አርግልኝ ) ፤

ንጹህ ፥ ልብን ፡ ፍጠርልኝ ( ፍጠርልኝ )

ለወንድሜ ፥ ታማኝ ፡ አርገኝ (ታማኝ ------ አርገኝ ) ።] /፪


am.mezmur.wikia.com

wikimezmur.org


thumb|400px|left|ቤትሌሄም (ቤቲ) ፡ ተዘራ - ንጹህ ፡ ልብ ፡ ስጠኝ ( Bethlehem Betty Tezera - Netsuh Leb SeTegne )