ይህ ፡ ድህረ-ገጽ ፡ ወደ ፡ WikiMezmur.org ፡ ተዘዋውሯል ። እባክዎን ፡ ይጎብኙት ። This website has been transferred to WikiMezmur.org, Please Visit. |
የሚረባኝን ፡ የሚያውቅልኝ /፪
ካንተ ፡ በላይ ፡ ማንም ፡ የለኝ
እኔ ፡ለራሴ ፡ ደካማ ፡ ነኝ
ካንተ ፡ በላይ ፡ ማንም ፡ የለኝ
እኔ፡ ለራሴ ፡ አቅምም፡ የለኝ
አፈርኩበት
እኔ ፡ አውቃያለው ፡ ባልኩበት /፪
አፈርኩበት
አስቢያለው ፡ ባልኩበት
አውቃያለው ፡ ባልኩበት
አሁንማ ፡ ካንተ ፡ ጋር ፡ ልስማማ /፪
እንግድማ ፡ ካንተ ፡ ጋር ፡ ልስማማ /፪
፩) ልጅ፡ አባቱን ፡ ዳቦ ፡ ቢለው
ድንጋይ ፡ ወስዶ ፡ እንዳይሰጠው ፣
ሰው ፡ መልካምን ፡ ማድረግ ፡ ካወቀ
እግዚአብሔር ፡ ፍቅርህ ፡ ከሰው ፡ የላቅ ። //፪
አሁንማ ፡ ካንተ ፡ ጋር ፡ ልስማማ /፪
እንግድማ ፡ ካንተ ፡ ጋር ፡ ልስማማ /፪
አፈርኩበት
እኔ ፡ አውቃያለው ፡ ባልኩበት /፪
አፈርኩበት
አስቢያለው ፡ ባልኩበት
አውቃያለው ፡ ባልኩበት ።
፪) ለቀኑ ፡ ክፋቱ ፡ ይበቃዋል
ነገም ፡ ስለራሱ ፡ ይጨነቃል ፣
እግዚአብሔር ፡ ያለው ፡ ነው ፡ የሚሆነው
ዝም ፡ ብሎ ፡ ያሱን ፡ ማዳን ፡ ማየት ፡ ነው ።
ነፍሴ ፡ አታውኪኝ ፡ አታስጨንቂኝ
ተይ ፡ ተይኝ ፣
እግዚአብሔር ፡ ያለው ፡ ይሁንልኝ
ይሁንልኝ ። //፪
፫) ነፍሴ ፡ ልምከርሽ ፡ ቁም ፡ ነገር
እግዚአብሔር፡ ስለሚወደው ፡ ነገር ፣
ፍቃዴ ፡ ይሁን ፡ በለሽ ፡ አትደምድሚ
ምን ፡ ይላል ፡ ጌታሽን ፡ ተስማሚ ።
ተይ ፡ነፍሴ ፡ ተይ ፡ ተይኝ ፣
አታስጨንቂኝ ፡ ተይኝ
አታስጨንቂኝ ፡ ተይኝ ። //፪
ተ----ይ ፡ ነፍሴ ፡ ተይ ፡ ተይኝ ፣
አታስጨንቂኝ ፡ ተይኝ ። /፪
ተ----ይ ፡ ኧረ ፡ ተይ ፡ ተይኝ ፣
አታስጨንቂኝ ፡ ተይኝ
አታስጨንቂኝ ፡ ተይኝ ።
ተይ ፡ ነፍሴ ፡ ተይ ፡ ተይኝ ፣ (በምረቱ : ቸርነቱ : የሚከልልሽ---)
አታስጨንቂኝ ፡ ተይኝ
ተይ ፡ ነፍሴ ፡ ተይ ፡ ተይኝ ፣ (እንደ-ንስር ፡ የሚያድስ ፡ ቃል ፡ ዋስ ፡ አለብሽ)
አታስጨንቂኝ ፡ ተይኝ (ኧረ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነዉ)
አታስጨንቂኝ ፡ ተይኝ ። (ታመኝዉ ፣ ታመኝዉ )
ተይ ፡ ነፍሴ ፡ ተይ ፡ ተይኝ ፣ (ታ----መኝዉ -----------)
አታስጨንቂኝ ፡ ተይኝ
ተይ ፡ ነፍሴ ፡ ተይ ፡ ተይኝ ፣ (ታ---መኝዉ ------------)
አታስጨንቂኝ ፡ ተይኝ ። መደብ:አማርኛ (Amharic) መደብ:ቤተልሔም (ቤቲ) ተዘራ ( Bethlehem (Betty) Tezera) መደብ:አማርኛ (Amharic) መደብ:ቤተልሔም (ቤቲ) ተዘራ ( Bethlehem (Betty) Tezera)