Mezmur Wiki
Register
Advertisement
ይህ ፡ ድህረ-ገጽ ፡ ወደ ፡ WikiMezmur.org ፡ ተዘዋውሯል ። እባክዎን ፡ ይጎብኙት ።
This website has been transferred to WikiMezmur.org, Please Visit.

የሉም ሲባል ይኖራሉ፣ ጠፉ ሲባል ይበዛሉ

ሲዋለዱ ብዙ መንታ ፣ ሩጫቸውን ማን ሊገታ

አይታክቱም ይሄዳሉ ፣ አይደክሙም ይበረታሉ

እንደ ንስር ይበራሉ ፣ እጥፍ ድርብ ያፈራሉ


እግዚአብሔር በልጁ ሞት የጠራዉ

ከነገድ ከቋንቋ ከህዝብ የዋጀዉ

ርስቴ ነህ ህዝቤ ገንዘቤ ያለዉ

ዓለም ምድረ በዳን በድል የመራዉ

የታደለ ምስጉን ነዉ


በሰው ብልሃት የተሰራ ፣ በሥጋ ደም የሚመራ

ሃሳቡን ለፍልስፍና ፣ እምነታቸው መች ሆነና

ይናገሩ ያዳናቸው ፣ እንደ ሰማይ ኳክብት ናቸው

ዲያቢሎስም ያውቃቸዋል ፣ ጊዜ ስጡኝ ይላቸዋል


እግዚአብሔር በልጁ ሞት የጠራዉ

ከነገድ ከቋንቋ ከህዝብ የዋጀዉ

ርስቴ ነህ ህዝቤ ገንዘቤ ያለዉ

ዓለም ምድረ በዳን በድል የመራዉ

የታደለ ምስጉን ነዉ


እሳት አለ በዉስጣቸው ፣ ማንም አይችል ሊያጠፋቸው

አይቻሉም ሲነኳቸው ፣ ተዋጊ ነው አምላካቸው

ሰባኪዎች በመገለጥ ፣ ለድያቢሎስ እሳት ረመጥ

ዘማሪዎች በበገና ይቀባሉ ገና ገና


እግዚአብሔር በልጁ ሞት የጠራዉ

ከነገድ ከቋንቋ ከህዝብ የዋጀዉ

ርስቴ ነህ ህዝቤ ገንዘቤ ያለዉ

ዓለም ምድረ በዳን በድል የመራዉ

የታደለ ምስጉን ነዉ


ሰይፍ አይዙም በእጃቸው ፣ የመንፈስ ነው መሳሪያቸው

እዩት እስቲ ይህን ምርኮ ፣ መንገደኛ አይደለም እኮ

የክርስቶስ ስም ያዳነው ፣ የካህናት መንግስት ነው

ያለም ብርሃን የምድር ጨው ፣ እንደ ኳክብት የተረጨው


እግዚአብሔር በልጁ ሞት የጠራዉ

ከነገድ ከቋንቋ ከህዝብ የዋጀዉ

ርስቴ ነህ ህዝቤ ገንዘቤ ያለዉ

ዓለም ምድረ በዳን በድል የመራዉ

የታደለ ምስጉን ነዉ


ሟርት አይሰራም በእስራኤል ፣ አስማት የለም በያቆብ ላይ

አይቆጠር ብዛቱ ፣ ድንበር የለው ለግዛቱ

እግዚአብሔር እፍ ያለበት ፣ የፈጠረው ለበረከት

መድሃኒት ነው መፈወሻ ፣ ወሰን የለው መጨረሻ


እግዚአብሔር በልጁ ሞት የጠራዉ

ከነገድ ከቋንቋ ከህዝብ የዋጀዉ

ርስቴ ነህ ህዝቤ ገንዘቤ ያለዉ

ዓለም ምድረ በዳን በድል የመራዉ

የታደለ ምስጉን ነዉ

am.mezmur.wikia.com

wikimezmur.org

thumb|400px|left|ታምራት ኃይሌ - የታደለ ምስጉን ነዉ ( Tamrat Haile - Yetadele Mesgun Newu ) መደብ:አማርኛ (Amharic)

Advertisement