FANDOM


ይህ ፡ ድህረ-ገጽ ፡ ወደ ፡ WikiMezmur.org ፡ ተዘዋውሯል ። እባክዎን ፡ ይጎብኙት ።
This website has been transferred to WikiMezmur.org, Please Visit.

ይነሳሉ /፬

በምድሪቱ ላይ ክፋት እርኩሰት ፣ አይሰለጥንም አዎ ፣ [አይሰለጥንም]/፪

በምድሪቱ ላይ ያመጻ ጉልበት ፣ አይሰለጥንም አዎ [አይሰለጥንም]/፪


ይነሳሉ /፫ ይነሳሉ /፫

[ላመጽ እርኩሰት ፣ እጅ የማይሰጡ

በእውነት በጽድቅ ፣ የሚገለጡ

በኃጢያት ግብዣ ላይ ፣ የማይገኙ

ያለምን ክብር ፣ የማይመኙ] /፪

ይነሳሉ /፫


ነብያቶችን በሰይፍ በስለት ፣ የጨረሰችው የጨረሰችው

ህዝበ እስራኤልን ጣኦት አምላኪ ፣ ያደረገችው ያደረገችው

እዩ ሲመጣ ፣ በበቀል ቅባት ፣ ሲገለጥበት ፣ ሲገለጥበት

ከሰገነቷ ፣ ድንገት ሳታስብ ፣ ፈጥኖ አስወገዳት


ይነሳሉ /፫ ይነሳሉ /፫

[ልክ እንደ እዩ ፣ ለጽድቅ የቀኑ

እንኤልዛቤልን ፣ የሚያስወግዱ

እምቢ አሻፈረኝ ፣ እምቢ የሚሉ

ለጌታ ደስታ ፣ ብቻ ሚኖሩ] /፪

ይነሳሉ /፫


" ልክ እንደ እዩ ለጽድቅ የቀኑ

እንኤልዛቤልን የሚያስወግዱ

እምቢ አሻፈረኝ እምቢ የሚሉ

ለጌታ ደስታ ብቻ ሚኖሩ

ይነሳሉ /፮ "


በሁለት ሐሳብ አያነከሱ

ሲጓዙ አይቶ ስጉአዙ አይቶ

ተነሳ አልያስ ለመወራርድ አምላኩን ጠርቶ

ሲገለጥለት የጠራው አምላክ ፣ ሰምቶ በእሳት ሰምቶ በእሳት

አስወገዳቸው ፣ ከምድሪቱ ላይ ፣ የባኦልን ነቢያት


ይነሳሉ /፫ ይነሳሉ /፫

[እንደ ኤልያስ ሚወራረዱ

እርሱ ብቻ ነው አምላክ የሚሉ

የቤቱ ቅናት የሚበላቸው

ክብሩን ለማየት ሚናፍቃቸው] /፪

ይነሳሉ /፫


ጻድቅ ሲቸገር ሰይፍ ሲበዛበት ፣ ኃጢያትን ጠልቶ ኃጢያትን ጠልቶ

አመጸኛው ገን ተከናውኖለት ፣ ሲኖር ተኩራርቶ ሲኖር ተኩራርቶ

ጽዋው ሲሞላ  ????? ????? ድንገት ሲነሳን ድንገት ሲነሳን

በአመጸኛው ሲፈረድበት ለጻዲቁ ግን ይፈርድለታል


ይነሳሉ /፫ ይነሳሉ /፫

[ላመጽ እርኩሰት እጅ የማይሰጡ

በእውነት በጽድቅ የሚገለጡ

በኃጢያት ግብዣ ላይ የማይገኙ

ያለምን ክብር የማይመኙ] /፪

ይነሳሉ /፫


am.mezmur.wikia.com

wikimezmur.org