Mezmur Wiki
Register
Advertisement
ይህ ፡ ድህረ-ገጽ ፡ ወደ ፡ WikiMezmur.org ፡ ተዘዋውሯል ። እባክዎን ፡ ይጎብኙት ።
This website has been transferred to WikiMezmur.org, Please Visit.

ከልጅነቴ ጀምሮ ፣ ገና ከሕጻንነት

[ያኔ የተሸከመኝ ፣ ያ ሰፊ ትከሻህ ፣ ዛሬም አልሰለቸኝ] /፪


በእድሜ ቀናቶቼ ፣ ሃዘን እንዳይገዛኝ

ምስጋናን ዝማሬን ፣ ለእኔ ሰጠህኝ

ትዝታዬ ሆነህ ፣ ምሕረትህ ለኔ

[ከእጅህ አልጣልከኝም ፣ ዛሬም ቢሆን ያኔ] /፪


ከልጅነቴ ጀምሮ ፣ ገና ከሕጻንነት

[ያኔ የተሸከመኝ ፣ ያ ሰፊ ትከሻህ ፣ ዛሬም አልሰለቸኝ] /፪


ከዘመናት በፊት ፣ ከእሩቅ ያወቅኅኝ

ገና ሳልፈጠር ፣ ዛሬን ያየህልኝ

ለዚያ ለጠላቴ ፣ በክፉ ላሰበኝ

[አሳልፈህ ለሞት ፣ መች እኔን ሰጠሀኝ ] /፪


ከልጅነቴ ጀምሮ ፣ ገና ከሕጻንነት

[ያኔ የተሸከመኝ ፣ ያ ሰፊ ትከሻህ ፣ ዛሬም አልሰለቸኝ] /፪


ስቀመጥ ስነሳ ፣ ሲጨልም ሲነጋ

ላፍታ ሳትለየኝ ፣ ሆነህ ከእኔ ጋር

እንደ አይንህ ብሌን ፣ ተጠነከክልኝ

[ማንም እንዳይነካኝ ፣ ትእዛዝህ ወጣልኝ] /፪


ከልጅነቴ ጀምሮ ፣ ገና ከሕጻንነት

[ያኔ የተሸከመኝ ፣ ያ ሰፊ ትከሻህ ፣ ዛሬም አልሰለቸኝ] /፪


በደሌ ከፍ ብሎ ሳለ ፣ ምሕረትህ በኔ ላይ ገነነ

እኔ ነኝ እግዚአብሔር የረዳኝ ፣ ከትቢያ ካመድ ላይ ያነሳኝ

እኔ ነኝ ጌታ የራራልኝ

እኔ ነኝ ጌታ ሰው ያረገኝ

እኔ ነኝ ይቅር የተባልኩኝ


ከልጅነቴ ጀምሮ ፣ ገና ከሕጻንነት

[ያኔ የተሸከመኝ ፣ ያ ሰፊ ትከሻህ ፣ ዛሬም አልሰለቸኝ] /፪

am.mezmur.wikia.com

wikimezmur.org


thumb|400px|left|አስፋው መለሰ - ከልጅነቴ ጀምሮ ( Asfaw Melesse - Kelejenetae Jem'ro (Jemero) ) መደብ:አማርኛ (Amharic) መደብ:አማርኛ (Amharic)

Advertisement