ይህ ፡ ድህረ-ገጽ ፡ ወደ ፡ WikiMezmur.org ፡ ተዘዋውሯል ። እባክዎን ፡ ይጎብኙት ። This website has been transferred to WikiMezmur.org, Please Visit. |
ልቤ ሰላም ሲያጣ ፣ መከራው ሲበዛ
ወደማን አያለሁ ፣ የሱስ ካንተ ሌላ
ልቤ ሰላም ሲያጣ ፣ ወጀቡ ሲበዛ
ወደ ማን አያለሁ ፣ የሱስ ካንተ ሌላ
ወየሁ ጠፋሁ ብዬ ፣ ሳለቅስ ሳነባ
ብቻዬን ነኝ ብዬ ፣ ስቆዝም ስከፋ
የዘላለም አምላክ የሱስ ደረሰልኝ
የልቤ ተናግሮ በሰላም ሂድ አለኝ
[አወድሃለሁ አወድሃለሁ አወድሃለሁ
ሚገባኝ እሄ ነው] /2
[ዝና ዝናዬ
ዝና ዝናዬ
አንተው ነህና ] /፪
ባገልግሎቴ ላይ ዝናዬ
ክብር ያሳየሀኝ ዝናዬ
የማዕረግ ልብሴ ፣ ዝናዬ
የክብር ሽልማት ፣ ዝናዬ
ብኖር ላትጠቀም ፣ ሞቼ ላትጎዳ
በደምህ ከፈልከው ፣ የሕይወቴን ዕዳ
በደለኛው ልቤን ፣ በደምህ ቀድሰህ
ሕይወትን ሸለምከኝ ፣ ደህንነት አልብሰህ
ጉድጓዴን ስቆፍር ፣ ድንበሬን ልገፋ
ምሕረትህ ገደበኝ ፣ ታዝቦ ስከፋ
ነፍሴም ተመለሰች ክርስቶስ?? አገዛት
በመስቀሉ ሥራ በጻድቁ ሞት
[አወድሃለሁ አወድሃለሁ አወድሃለሁ
ሚገባኝ እሄ ነው] /፪
[ዝና ዝናዬ
ዝና ዝናዬ
አንተው ነህና ] /፪
ባገልግሎቴ ላይ ዝናዬ
ክብር ያሳየሀን ዝናዬ
የማዕረግ ልብሴ ዝናዬ
የክብር ሽልማት ዝናዬ
የሰጠንን ላታ የእጁን ተመኝቼ
ምሕረትን ስጠማ ፣ ፍሬዋን በልቼ
የጽድቅን ጥያቄ በልጁ መልሶ
ፈቃዱን አጸና ፣ መርገሜን ፈውሶ
[ዝና ዝናዬ
ዝና ዝናዬ
አንተው ነህና ] /፪
ባገልግሎቴ ላይ ዝናዬ
ክብር ያሳየሀን ዝናዬ
የማዕረግ ልብሴ ዝናዬ
የክብር ሽልማት ዝናዬ
am.mezmur.wikia.com
wikimezmur.org
መደብ:አማርኛ (Amharic) መደብ:Yossef kassa