ይህ ፡ ድህረ-ገጽ ፡ ወደ ፡ WikiMezmur.org ፡ ተዘዋውሯል ። እባክዎን ፡ ይጎብኙት ። This website has been transferred to WikiMezmur.org, Please Visit. |
በክብረ ልዘምር በገናየን ላንሳ
ማምለጥ ሆኖልናል ካንተ የተነሳ
እንደ ጠላት ሃሳብ በኔ ላይ አልሆነም
[ከፍ አደርግሃለሁ ክበር ለዘላለም] /፪
ፍቅርህ ያስገርመኛል /፪
እኔን ሰው አድርጎናል
ቃልህ ያስደንቀኛል /፪
እኔን አስመልጦኛል
ጠላት መርዶውን ሰምቷል /፫
ጠላት ማምለጤን አይቷል /፫
ጠላት መክበሬን ሰምቷል /፫
ከፍታዬን ሰምቶ መርዶ ሆኖበታል
ውርደቴን ሲጠብቅ ታሪክ ተገልብቷል
ከኔ ጋር እንዳለህ ፍጥረት ሁሉ አይቷል
[አምላኬ ቅናትህ ይህንን አድርጉአል????] /፫
[ለኔ መልካም የሚሻ አለኝ
መልካም አባት ከላይ አለኝ] /፪
[ለኔ መልካም የሚሻ አለኝ
መልካም ወዳጅ የሱስ አለኝ] /፪
በረከቴን አይቶ በቀል ያሰበውን
የእኔን መዋረድ ውድቀት ያለመውን
ጠላቴን ከእግሬ ስር ጌታዬ ጣልክና
እኔን ግን አቆምቀን በብዙ ምስጋና /፪
እኔን ግን አቆምቀን በድል እንደገና
ፍቅርህ ያስገርመኛል /፪
እኔን ሰው አድርጎናል
ቃልህ ያስደንቀኛል /፪
እኔን አስመልጦኛል
ጠላት መርዶውን ሰምቷል /፫
ጠላት መዳኔን አይቷል /፫
ጠላት መሾሜን አይቷል /፫
ከጉባኤ ሸሽተው ርቀው የምያዝኑትን
እሰበስባለሁ እንዳልክ ካንቺ የሆኑትን
ስድብ እንደሸክም ከብዶባቸው ነበር
ዛሬ ግን አበቃ ተሰብሯል ያ ቀምበር /፫
በነጻነት ያመልካሉ
ክብርን ላንተ ይሰጣሉ
[ተጥሏል የሚከሳቸው
ጧት ማታ ያስለቀሳቸው] /፪
ደካማ ከሆነ ከተናቀው ጉልበት
ብርቱ ራአይ ወጣ አንተም ከበርክበት
የሚያዩኝ በሙሉ እየተገረሙ
በብዙ አምልኮ ምስጋናን አሰሙ
በብዙ ዝማሬ ምስጋናን አሰሙ
በብዙ እልልታ ምስጋናን አሰሙ
ፍቅርህ ያስገርመኛል /፪
እኔን ሰው አድርጎናል
ቃልህ ያስደንቀኛል /፪
እኔን አስመልጦኛል
ጠላት መርዶውን ሰምቷል /፫
ጠላት ማምለጤን አይቷል /፫
ጠላት መክበሬን ሰምቷል /፫
am.mezmur.wikia.com
wikimezmur.org
thumb|400px|left|ያሬድ ፡ ማሩ - ጠላት ፡ ማምለጤን ፡ አይቷል ( Yared Maru - Telat MamleTen Aytual ) መደብ:አማርኛ (Amharic)