Mezmur Wiki
Advertisement
ይህ ፡ ድህረ-ገጽ ፡ ወደ ፡ WikiMezmur.org ፡ ተዘዋውሯል ። እባክዎን ፡ ይጎብኙት ።
This website has been transferred to WikiMezmur.org, Please Visit.

ስጋት አይገባኝም ፣ አንተ ያለህ ጎኔ

እጄን ይዘኅዋል ፣ ላትጥለኝ መድህኔ

ስምህ ጋሻዬ ነው ፣ ክፉን ምመታበት

ለኔ ደግሞ ፣ ጥላ የምሸሸግበት


[እፎይ ብያለሁ ፣ እርፍ ብያለሁ

ጌታ ፣ የኔ ባለዉለታ] /፪


ምስጋና ይገባሃል ፣ የኔ ጌታ ፣ ኦኦኦኦ

ስለሆንክልኝ ፣ የነፍሴ ባለዉለታ

ከስንቱ ማጥ አወጣኅኝ

ከስንቱስ አደጋ አዳንከኝ

[እረ ምን ልበል ፣ ተመስገን ከማለት በቀር ፣ ምን ልክፈልህ ] /፪


የታሰርኩበትን ፣ ገመዴን በጥሰህ

የተጫነብኝን ፣ ቀንበሩን ሰብረህ

ይፍታህ ብለህ ፈተህ ፣ ነጻ አውጥተኅኛል

በዘላለም ኪዳን ልጅህ አርጌኅኛል


[እፎይ ብያለሁ ፣ እርፍ ብያለሁ

ጌታ ፣ የኔ ባለዉለታ] /፪


ምስጋና ይገባሃል ፣ የኔ ጌታ ፣ ኦኦኦኦ

ስለሆንክልኝ ፣ የነፍሴ ባለዉለታ

ከስንቱ ማጥ አወጣኅኝ

ከስንቱስ አደጋ አዳንከኝ

[አረ ምን ልበል ፣ ተመስገን ከማለት በቀር ፣ ምን ልክፈልህ ] /፪


ከጣራዬ በታች ፣ በጓዳዬ ገብተህ

አበጃጀህልኝ ፣ ጎዶሎዬን ሞልተህ

ዝርግፍ ጌጤ ለኔ ፣ ዉበት ደም ግባቴ

ባንተ አማረብኝ ፣ አረፈች ሕይወቴ


[እፎይ ብያለሁ ፣ እርፍ ብያለሁ

ጌታ ፣ የኔ ባለዉለታ] /፬


am.mezmur.wikia.com wikimezmur.org Amharic Mezmur thumb|400px|left|ዮሴፍ በቀለ - እፎይ ብያለሁ ( Yosef bekelet - Efoy Beyalehu ) መደብ:አማርኛ (Amharic) መደብ:አማርኛ (Amharic)

Advertisement