ይህ ፡ ድህረ-ገጽ ፡ ወደ ፡ WikiMezmur.org ፡ ተዘዋውሯል ። እባክዎን ፡ ይጎብኙት ። This website has been transferred to WikiMezmur.org, Please Visit. |
[በቅፍህ መሃል ፣ ስፍራን ሰጠኅኝ ፣ ተደላድዬ
እፎይ ብያለሁ ፣ አንተን አግኝቼ ፣ ክበር ጌታዬ
እንዳልታወክ በቀኜ አለህ ውስጤ መች ሰግቶ
ልቤም ይጣራል ፣ የሱስ እያለ ፣ በፍቅርህ ነዶ] /፪
እየሱስ ፣ ለህይወቴ ትርጉም [እየሱስ ፣ የሆንክልኝ ፍቺ] /፪
እየሱስ ፣ ክብርን አይቻለሁ [እየሱስ ፣ እኔስ ባንተ እጂ] /፪
ሁሉን ቻይ አምላክ ፣ ወረት የማታውቅ ፣ እሩህሩህ ጌታ
ፍቅርህ ማረከኝ ፣ ያንተ እንድሆን ፣ ልቤም ተረታ
ሌላ አይገዛንም ፣ ካንተ በስተቀር ፣ በምድር ያለው
ሁሉ የሞላህ ፣ ባለ ጸጋ አምላክ ፣ አንተን ይዣለሁ
[ክበርልኝ] /፫ አላየሁም ካንተ የምበልጥብኝ
[ንገስልኝ] /፫ አልሰማሁም ካንተ የምበልጥብኝ
[አላየሁም ካንተ የምበልጥብኝ
አልሰማሁም ካንተ የምበልጥብኝ] /፪
ስትሾም ስትሸልም አቤት ስታውቅበት
ደርሰህ ብርሃን ስትሆን ቀን ለጨለመበት
[ስታውቅበት ፣ ማበጃጀት
ስታውቅበት ፣ መልክ መስጠት
ስታውቅበት ፣ መሸላለም
ማንም እንዳንተ የለም] /፪ (ከተከስተ ጌትነት ጋር)
እየሱስ ፣ ለህይወቴ ትርጉም [እየሱስ ፣ የሆንክልኝ ፍቺ] /፪
እየሱስ ፣ ክብርን አይቻለሁ [እየሱስ ፣ እኔስ ባንተ እጂ] /፪
እየሱስ ፣ ለህይወቴ ትርጉም [እየሱስ ፣ የሆንክልኝ ፍቺ] /፪
እየሱስ ፣ ክብርን አይቻለሁ [እየሱስ ፣ እኔስ ባንተ እጂ] /፪
am.mezmur.wikia.com wikimezmur.org Amharic Mezmur
thumb|400px|left|ፓስተር ካሳሁን ለማ - የሕይወቴ ትርጉም ( Pastor Kassahun Lemma - YeHeywetae Tergum ) መደብ:አማርኛ (Amharic)